ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማሻሻልና ሁሉን ዐቀፍ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የኢትዮጵያ ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ተግባራዊ መሆኑን የትራንስፖርት ሚስስትሯ ክብርት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አስታወቁ።
ስትራቴጂው በውስጡ ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት ውስጥ የምትተገብራቸውን እርምጃዎች በዝርዝር ያስቀመጠ ነው ተብሎለታል።
ሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ከ2013 ዓ.ም እስከ 2022 ዓ.ም የሚገልፅ ማብራሪያ ሲሰጥ፤ አገልግሎቱ ኅብረተሰቡ በቀላሉ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል፣ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ እና ወደ ብዙኃን ትራንስፖርት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያደርግ መሆኑን ሰምተናል።
የማኅበረሰቡ ጤናም እንዲጠበቅ የበኩሉን አስተዋጽዖ የሚያበረክት የትራንሰፖርት ዘርፍ መሆኑን ያመላከቱት ሚኒስትሯ፤ ስትራቴጂው ስኬታማ እንዲሆን አስተዋፆኦ ላበረከቱት ለአይቲዲፒ, ዩኤን-ኢፒ, ዩኤን-ሃቢታት እንዲሁም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።