ግንባታው በፍ/ቤት ከተገደ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ላይከበር ይችላል 

ግንባታው በፍ/ቤት ከተገደ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ላይከበር ይችላል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የቤቶች ኮርፓሬሽን ካሳ አልተከፈለኝም በሚል የመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት በፍርድ ቤት ለ 3 ወር እንዲታገድ ሊያደርግ በመሆኑ የመስቀል በዓል በሥፍራው ላይ እንዳይከበር ሊያደርገው እንደሚችል በመነገር ላይ ነው።

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በፕሮጀክቱ ለሚፈርሱ ቤቶች ካሳ አልተከፈለኝም በሚል ክስ የፕሮጀክቱ ግንባታ ለ 3 ወራት እንዲቆም በፍርድ ቤት አስወስኗል።
ፕሮጀክቶቹ የሚነካቸው ባለቤትነታቸው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሆኑ17 ቤቶች ያሉ ሲሆን፤ 7ቱ በቅርስነት የተመዘገቡ በመሆናቸው፤ በመልሶ ግንባታውና በማስዋብ ዲዛይኑ ውስጥ ተካተው እንዲታደሱ መወሰኑን አስተዳደሩ በተለያየ ጊዜ ለከተማ አስተዳደሩ ማሳወቁ አይዘነጋም።
በሌላ በኩል  ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በኩል የሚወጡ ጥቆማዎች፤ መስተዳድሩ  በቅርስነት ከተመዘገቡ ውጪ  ላሉ 10 የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ካሳ መከፈሉን ያሳያሉ።

LEAVE A REPLY