ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ምጣኔ ሀብቷ 5.6 በመቶ ሊጎዳ ይችላል ተባለ

ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ምጣኔ ሀብቷ 5.6 በመቶ ሊጎዳ ይችላል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? በሚለው ዙሪያ ጥናት ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ የኮሮና ቫይረስ በዚሁ ከቀጠለ ኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብቷ ክፉኛ ሊጎዳ ይችላል ብለዋል።

አውሮፓ እና አሜሪካ እንደተስፋፋው፤ ቫይረሱን እኛም አገር ቢሰራጭ ኢኮኖሚያችን እርሱን የሚሸከምበት አቅም ስለሌለው ከሚጠበቀው በላይ ይጎዳናል ያሉት ምሁር ምዕራባውያን አገራት የተሻለ ኢኮኖሚ፣ የሰው ኃይል እና ቁጠባ አላቸው፣  እኛ ዘንድ እንዲህ ዓይነት ዕድል አለመኖሩ ችግሩ ጥልቅ  እንደሆነ በምክንያትነት ያቀርባሉ።
 ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ የበጀት ዓመት የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) በአማካይ 11.2 በመቶ ሊላሽቅ ይችላል በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2013 በሚዘልቀው የበጀት ዓመት ላይ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሚገታ ከሆነ፤ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ ሊቀንስ የሚችለው በ5.6 በመቶ እንደሆነ ጠቁመው፤ በአንጻሩ የሚያስከትለው ጉዳት  እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት ከዘለቀ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ የሚቀንሰው በ16.7 በመቶ ነው ሲሉ ያብራራሉ።
 ያለንን ኃይል በማሰባሰብ ቫይረሱ ወደ ኅብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በፊት በቁጥጥር ሥር ማድረግ፤ የቫይረሱ መስፋፋት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ድቀት ለመቀነስ መፍትኄ እንደሆነም ፕሮፌሰር አለማየሁ ጠቁመዋል።
በውጪ ሀገራት ያሉ ዘመዶቻችን በባንክ በኩል የሚልኩት ገንዘብ አገሪቱ ምርት ወደ ውጪ ልካ ከምታገኘው ዶላር በላይ መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ፤ “የመንግሥት አሃዞችን ብንመለከት እንኳ፣ አገሪቱ ወደ ውጪ አገራት ምርት ልካ የምታገኘው ገቢ 2.8 እስከ 3 ቢሊዮን ነው። እንደውም ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እየቀነሰ ነው” ሲሉም አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY