በግድያ ወንጀል የተሠማሩ 48  የአባ ቶርቤ እና የሸኔ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በግድያ ወንጀል የተሠማሩ 48  የአባ ቶርቤ እና የሸኔ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በግድያና ዘረፋ ወንጀል ተሰማርተዋል የተባሉ 48 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

በክልሉ የተለያዮ አካባቢዎች ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ኃይል በማዕከላዊ መንግሥት ሥልጣን ተነጠቅኩ በሚል አካል የሚመራ ነው ያለው ኮሚሽኑ፤ በኦነግ ሸኔ ቡድን የሚመራው የአባ-ቶርቤ የግድያ አደረጃጀት ከ2009 ዓ.ም ወዲህ በከተሞች ብቻ ከ114 ሰዎች በላይ ሕይወት ቀጥፏል ብሏል።
 የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የምርመራና ፍትህ ማሰጠት ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ግርማ ገላን በነቀምቴ፣ በቀለም ወለጋ፣ በቡራዩ እና በሌሎችም ስፍራዎች በወንጀሉ ሰንሰለት የተሰማሩትን በማስረጃ የማጣራቱ ሥራ በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል።
አባ ቶርቤ በሚል ስም የመንግሥት ባለሥልጣናትና በርካታ ዜጎችን በመግደል ተግባር የተሰማራው ቡድን በኦነግ የሚመራ ሆኖ በሃገር ውስጥና በውጭ በዚሁ ሥልጠና የወሰዱ መሆናቸው ተገልጿል።
ቡድኑ እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ታዳጊዎችን ከትምህርት ቤት አታለው በማስወጣት ጫካ ወስዶ ማሰልጠን፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን በየከተማው አድኖ መግደል፣ የሃሰት መረጃና ፕሮፓጋንዳን የሚነዙ የማኅበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎችን መልምሎ ማሰማራት እና በቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫ ከቡድኑ ውጭ ማንም የሚያሸንፍ ከሆነ ነፍጥን የማንሳት ዘመቻን ወጥኖ መንቀሳቀስ የቡድኑ ዋነኛ ዓላማዎች ናቸው ተብሏል።
ይህ ቡድን  እስከ አዲስ አበባ ድረስም ሰንሰለቱን ዘርግቶ መቆየቱንና ከፌዴራል ፖሊስና ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ጋር በተደረገ ቅንጅታዊ ሥራ አባላቱ  እስከነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ከመግለጫው መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY