ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል፤ በስልጤ ዞን፣ ስልጢ ወረዳ “ሰነና ገሬራ ” ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ዜኖ ሸምሱ፤ ትላንት ቅበት በተሰኘው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አራት ልጆችን መውለዷ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።
ግለሰቧ ምጥ ይዟት ሆስፒታል ከደረሰች በኋላ በተደረገላት የቀዶ ሕክምና 3 ሴት እና 1 ወንድ ልጅ በሰላም መገላገሏን የተናገሩት የሕክምና ባለሙያዎች፤ በአሁኑ ሰዐት 4ቱም ሕጻናት በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑን፣ አራት መንትዮችን በሰላም የተገላገለችው የ30 ዓመቷ ወ/ሮ ዜኖ በአስተማማኝ ጤንነት ላይ እንደሆኑ አስረድተዋል።