በኦሮሚያ ክልል 210 ሰዎች ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በኦሮሚያ ክልል 210 ሰዎች ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በክልሉ ለረጅም ጊዜ በድብቅ ሲፈፀም ከነበረው የመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ባለፉት ቀናት በተደረገ ኦፕሬሽን፤ ከ210 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፣ የሕዝብ እና የመንግሥት ገንዘብ ወደ መንግሥት ካዝና እንዲመለስ መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ዳንኤል አሰፋ  ተናግረዋል።

ግለሰቦች በብዙ ሰው ስም በመደራጀት እና በተለያየ ዓይነት ማጭበርበር የተወሰደ ከ376 ሺኅ በላይ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ማዳን ተችሏል ያሉት የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ ከሰብኣዊ መብት አያያዝ ጋር በተገናኘም ታራሚዎች ላይ ያልተገባ አያያዝ ያደረጉ ከ30 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንደ ዋሉ  አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY