ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በኮረና ሳይሆን በግፍ ነው ሲል ጥበቃው ተናገረ 

ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በኮረና ሳይሆን በግፍ ነው ሲል ጥበቃው ተናገረ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በነጭ ፖሊስ በግፍ ለተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ደማቅ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተደረገለት።

“ደንበኛዬን ለሞት ያበቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ነው ይላሉ፤ በዘረኝነት ወረርሽኝ መሞቱን ማን በነገራቸው?” የሚል አሳዛኝና ጠጣር ንግግር ያደረገው የሟች ጠበቃ የብዙኃኑን የሰው ልጆች እውነተኛ ስሜት የሚኮረኩር መሳጭ መልዕክት በሽኝቱ ላይ አስተላልፏል።
በሟች ጆርጅ ፍሎይድ የሽኝትና መታሰቢያው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ ሁሉ ተነስተው እንዲቆሙና ለ8 ደቂቃ ከ46 ሴኮንዶች የሕሊና ጸሎት እንዲያደርጉ ተደርጓል።
ይህ ድርጊት ግፍ ፈጻሚው ነጭ  የፖሊስ ባልደረባ ዴሪክ፤ ሟች ፍሎይድ አንገት ላይ በጉልበቱ ቆሞ ትንፋሹን እስኪያጣ የቆየበትን የጭንቅና የጣር ጊዜ ለመዘከር ያለመ ነው ተብሎለታል።
ባልተጠበቀ መንገድ ሕይወቱን ያጣው የሟች ጆርጅ ፍሎይድ የሕይወት ታሪክ። በታዋቂው የጥቁር መብት ተሟጋች ሬቭ አል ሻርፐን አማካኝነት የተነበበ ሲሆን፤ ስመ ገናናው የጥቁር መብት ተሟጋች አል ሻርፐን ባደረጉት ንግግር “በመላው አሜሪካ የምትገኙ ጥቁር ወንድሞቼ፣ አሁን ሁላችንም ከአንገቴ ጉልበትህን አንሳልኝ የምንለበት ሰዓት ላይ ደርሰናል” ሲሉም ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY