ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኒውዚላንድ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ የከረመ የመጨረሻው ግለሰብ ማገገሙን ተከትሎ፣ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከተገኘ 17 ቀናት አልፏል ተብሏል።
አገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ማስቆም ችላለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርዴርን ቐ፤ ይሁን እንጂ ውጤቱ እንዳይቀለበስ እና ወረርሽኙ እንዳያገረሽ ነቅተን ልንዘጋጅ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
ኒውዚላንድ ከውጭ ተመላሽ ለሆኑ ዜጎች እና ቋሚ ነዋሪዎች ካልሆነ በስተቀር ድንበሯን ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ም ጥብቅ ውሳኔ ሰጥታለች።