የህዳሴው ግድብ በሱዳንና በግብፅ ከሚገኙ ግድቦች የተሻለ መሆኑን የሱዳኑ ሚኒስትር መሰከሩ

የህዳሴው ግድብ በሱዳንና በግብፅ ከሚገኙ ግድቦች የተሻለ መሆኑን የሱዳኑ ሚኒስትር መሰከሩ

????????????????????????????????????

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየህዳሴው  ግድብ ከደህንነት አኳያ በሱዳን እና ግብፅ ውስጥ ካሉ ግድቦች የተሻለ መሆኑን የሱዳን የመስኖ እና ውሃ ሃብቶች ሚኒስትር ያሲር አባስ ተናገሩ።

“አንዳንድ ጥናቶች የህዳሴው ግድብ ከደህንነት አኳያ ከሱዳን ግድቦችና ከግብፅ ከፍተኛ ግድብ የተሻለ ነው” ሲሉም ሚኒስትሩ ግድቡ ያረፈበት ሥፍራ ለሱዳን ካለው ቅርበት አንጻር ያለውን ጠቀሜታ አመላክተዋል።
እኛ ከራሳችን ፍላጎት ጋር የምንቆም እንደመሆኑ መጠን፣ የህዳሴው ግድብ ለእኛ ይጠቅመናል ስንል ከኢትዮጵያ ጋር ወገናችሁ የሚል አቤቱታ ይቀርብብናል ብለዋል ሱዳኑ የመስኖና ዉሃ ሀብት ሚኒስትር።
ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ በርካታ ውይይቶችን ለዓመታት ሲያደርጉ መቆየታቸውንና ይሄ ሰላማዊ መንገድ ወደ ፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY