በኦሮሚያ ፣ በትግራይ፣ በደቡብና ሐረሪ ክልሎች በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው

በኦሮሚያ ፣ በትግራይ፣ በደቡብና ሐረሪ ክልሎች በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ከተደረገው 48 የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰው የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ በክልሉ ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 17 ደርሷል።

የላቦራቶሪ ምርመራው የተደረገው በሀረማያ ዩኒቨርሲቲና በሀረሪ ክልል ላቦራቶሪ ሲሆን፣ የእለቱ ታማሚ ተጋላጭነት ሁኔታ የታወቀ ንክኪ ያላቸው ሲሆን፤  የሐኪም ወረዳ እና  የሽንኮር ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የ54 ዓመት ሴትና የ25 ዓመት ወንድ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች መንግሥት 476 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አንድ የ25 ዓመት  የሀዋሳ ከተማ ነዋሪበኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።
ወጣቱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ቢሆንም፤ በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ወይም ንክኪ እንዳለው የክልሉ ጤና ቢሮ አረጋግጫለሁ ብሏል።
በሌላ በኩል ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ባሳየባት ትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 79 መድረሱ ተሰምቷል።
በክልሉ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ207 (ለሁለት መቶ ሠባት ሰዎች) በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ   ሠባት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጠቆመው የክልሉ መንግሥት መግለጫ፤ ከሠባቱ ሰዎች መካከል ሁለቱ  የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ ሦስቱ ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው፤ እንዲሁም የተቀሩት ሁለቱ  የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ብሏል።
 በኦሮሚያ ክልል ውስጥ 519 ሰዎች በተደረገ  የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ  ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል።
በክልሉ በቫይረሱ ከተያዙት መሀል የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሐረርጌ ነዋሪና የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፣ የ10 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሐረርጌ ነዋሪና የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፣ የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሐረርጌ ነዋሪና የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፣ የ12 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሐረርጌ ነዋሪና የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፣ የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰንዳፋ ቤኬ ነዋሪና የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፣  የ3 ዓመት ህፃን ኢትዮጵያዊ የጉጂ ነዋሪ ይገኙበታል ተብሏል።

LEAVE A REPLY