የአ/አ ዩኒቨርሲቲ ማቆያ ከውጭ የሚመጡ 1ሺኅ 200 ሰዎች እንደሚገቡበት ተሰማ 

የአ/አ ዩኒቨርሲቲ ማቆያ ከውጭ የሚመጡ 1ሺኅ 200 ሰዎች እንደሚገቡበት ተሰማ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማቆያ ማዕከሉ የኮሮና ቫይረስ አዲስ መመርመሪያ ማዕከል ከፍቻለሁ አለ።

የኮሮና ቫይረስ ውጤት ማሳያ መሣሪያዎቹ በአንድ ጊዜ 93 ናሙናዎችን በመመርመር በ2 ሰዐት ከ30 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ውጤቱን እንደሚያሳዩ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ታረቀኝ ብርሃኑ ተናግረዋል።
በዓለም የጤና ድርጅት እውቅና ያገኘው ማሽኑ ለጊዜው በ5 ባለሙያዎች በቀን ከ100 እስከ186 ናሙና ውጤት እንደሚያሳይም ነው የተነገረው።
ዛሬ ማዕከሉን በይፋ ያስከፈቱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን እየሠራቸው ባሉ ተግባራት ሃገራዊ ጫናዉን እያቀለለ መሆኑን እና  በዛሬው ቀን ከውጭ ሃገር የሚመጡ 1ሺኅ 200 ሰዎች ለ14 ቀናት በዩኒቨርሲቲው እንደሚቆዩ፣ ሙሉ ምርመራም እንደሚደረግላቸው  ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የምርመራ ማዕከሉ ቀደም ሲል የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ የሚወስደውን ጊዜ 50 በመቶ እንደሚቀንስ የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ ሌሎች ግብዓቶችም እንደሚሟሉ ለዩኒቨርሲቲው ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከዚህ ቀደም በመጀመሪያ ዙር ለ1ሺኅ 700 ሰዎች የለይቶ ማቆያ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ለ1ሺኅ 200 ሰዎች የለይቶ ማቆያ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የዮንቨርስቲው የሕዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበቀ ዱቶሮ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY