የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው 1ሺኅ ዜጎች በአ/አ እንዳሉ ተሰማ

የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው 1ሺኅ ዜጎች በአ/አ እንዳሉ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዜጎች እርዳታና በተለያዮ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጎማ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚገኙ የኩላሊት ታማሚዎች የሚያደርጉት የዲያሊስስ ሕክምና በኮሮና ምክንያት ከባድ ችግር ተጋርጦበታል ተባለ።

በኩላሊት ሕመም የተጠቁ አባላቱን በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጠንካራ ድጋፍ ዲያሊሲስ ሲያደርግ የቆየው የኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት አሁን ላይ በችግር ውስጥ እገኛለሁ ብሏል።
በዚህ ወቅት የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ነገር ግን ሕክምናውን ያልጀመሩ በአዲስ አበባ ብቻ 1 ሺኅ ዜጎች አሉ ሲል አመላክቷል።
የኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ማኅበሩ ውስጥ 67 የሚሆኑ ሕሙማንን በቋሚነት እንደሚደግፍ ገልጸው፤ ከዚህ በተጨማሪ በመንግሥት 100 የሚሆኑ ሕሙማን ለአንድ ዓመት የነፃ ሕክምና እንዲያገኙ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል ማስቻሉን ተከትሎ በአጠቃላይ 167 ሰው  እየተደገፈ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

LEAVE A REPLY