ጃዋር መሐመድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊታሰር ይችላል ተባለ

ጃዋር መሐመድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊታሰር ይችላል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጃዋር መሀመድ የክልልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማደፍረስ፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ድኅረ-ገፆች ከሚለጥፋቸው የተዛቡ መረጃዎች እንዲታቀብ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስጠነቀቀ።

ግለሰቡ እስከ አሁን በለቀቃቸው ከእውነታ የራቁ መረጃዎች በሕግ የሚጠየቅ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ መግለፁን ተከትሎ ጃዋር በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊታሰር እንደሚችል የተለያዮ ምንጮች እየገለፁ ናቸው።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ሰኔ 2/2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ ኮሚሽኑ ወንጀልን ከመከላከል፣ የክልልሉን ሰላም እና ፀጥታ ከማስከበር፣ እንዲሁም ሕግ እና ሥርዓትን ከማስከበር የዘለለ ተግባር እንደሌለው አስታውሶ፤ በዚህም መሠረት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ልዩ ኃይሉን በማደራጀት ፣ የሕዝቡን ሰላም እና የክልልሉን ፀጥታ በማስጠበቅ ላይ ይገኛል ብሏል።
 ይህንን የክልልሉን ሰላም እና መረጋጋት የማይሹ አንዳንድ ግለሰቦች እና ቡድኖች፣ የሕዝብ መከታ የሆነውን ኃይል ሥም በማጠልሸት፣ የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ያለው መግለጫ፤ ከአሁን በኋላ ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ቡድን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን መልካም ስም እና ዝና እንዲያጎድፍ ፣ ለፖለቲካ ትርፍ እንዲጠቀምበት ፈጽሞ እድል አንሰጥም ሲል አስታውቋል።
“ከዲንሾ ጋር ተያይዞ የሚሰራጨው ተራ አሉባልታም ሊገታ ይገባዋል፡፡ መነሻው የግለሰቦች ፀብ ሲሆን ጉዳዩ በህግ ተይዞ በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ግለሰቦች በተለይም ጃዋር መሀመድ፣ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የተዛባ መረጃን በመለጠፍ ብዙዎችን የማሳሳት ተግባሩን የቀጠለ ሲሆን፣ በእንግሊዘኛ የለጠፈውን እንዲሁም ሌሎች ተጨባጭ መረጃዎችን በማያያዝ በሕግ አግባብ የምንጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን” በማለት በጃዋር መሐመድ ላይ ቆፍጠን ያለ አቋም መውሰዱን ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY