ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዐታት በተደረገ የላብራትሪ ምርመራ 6ሺኅ 187 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ።
ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ከ2 እስከ 115 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ 93 ወንድና 77 ሴቶች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የጠቆመው የጤና ሚኒሴቴር መግለጫ፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 57 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 13 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል እና 7 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ እና 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው ሲል ይፋ አድርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬም ሦስት ሰዎች (ሁለት ከአዲስ አበባ፣ አንድ ከኦሮሚያ ክልል) ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 36 መድረሱን ለማወቅ ተችሏል።
በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 2ሺኅ 068 ሲሆን፣ 33 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፤ ትላንት ከአዲስ አበባ ተጨማሪ 22 ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው፣ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 401 ሰዎች ደርሷል ብሏል።