የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ ኢትዮጵያ አቋሟን ይፋ አደረገች

የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ ኢትዮጵያ አቋሟን ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን እያካሄዱት ባለው የሦስትዮሽ ድርድ ላይ ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ላይ ያላትን አቋም አስታውቃለች።

ጉዳዮን አስመልክቶ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በሁለተኛ ቀን ውይይት ኢትዮጵያ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያላትን አቋም ግልፅ አድርጋለች ብሏል።
በህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን መመሪያዎች ዙሪያ እውነተኛ የሆነ ውይይት እና ድርድር ለማድረግ ያላትን ቁርጠኛ አቋም የገለፀችው ኢትዮጵያ፤ በ በሦስቱ ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች ደረጃ ዳግም የተጀመረውን ውይይት በመልካም ጎኑ እንደምትመለከተው ይፋ አድርጋለች።
የታዛቢዎች ሚና ከታዛቢነት ሊያልፍ እንደማይገባ በመጠቆም፣  አደራዳሪ አካል እና ተሞክሮዎችን እንዲያካፍሉ ከተፈለገም ሦስቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ ደርሰው ጥያቄ ሲያቀርቡ ብቻ መሆን እንደሚገባ ኢትዮጵያ ገሀድ ባወጣችው አቋሟ ላይ አስነብባለች።
የሦስቱ ሀገራት የህግ እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ከየካቲት 4 እስከ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ ያቀረቡት ሰነድ የድርድሩ መሰረት ሊሆን ይገባል ያለችው ኢትዮጵያ፤ ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን መመሪያን በተመለከተ የራሷን አማራጭ ማቅረቧን፣ ሱዳንም አቋማን የሚያንፀባርቅ ሰነድ ማስገባቷን ጠቁማለች።
ኢትዮጵያ በሶስትዮሽ ውይይቱ በሁሉም አካላት ዘንድ መተማመን ሊኖር እንደሚገባ የፀና እምነት እንዳላት የገለጸችው ኢትዮጵያ፤ ይህም የሦስትዮሽ ድርድሩ የተሳካ እንዲሆን ለማስቻል ከመሻት መሆኑን ብታመላክትም፣ ግብፅ አሁን እየተካሄደ ባለው የሦስትዮሽ ውይይት ላይ እያንፀባረቀች ያለው አቋም እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዐት ለሁለተኛ ጊዜ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የውጭ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲፈጠር እያደረገች ያለው ጥረት በድርድሩ ላይ  መተማመን እንዳይኖር አድርጓል ብላለች።

LEAVE A REPLY