ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ዛሬ ስብሰባ የተቀመጠው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን አፅድቋል።
ፓርላማው 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥልቀት ተወያይቶበታል።
በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በአንድ ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምጽ፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በ2 ተቃውሞ፣ በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ እንደፀደቀው ታውቋል።