ሳዑዲ ሦስቱ ሀገራት በህዳሴው ግድብ ላይ ልዮነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ ድጋፍ አደርጋለሁ አለች

ሳዑዲ ሦስቱ ሀገራት በህዳሴው ግድብ ላይ ልዮነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ ድጋፍ አደርጋለሁ አለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ሳዑዲ አረቢያ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ሦስቱ ሀገራት ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች።

በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላሂ፤  ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው  ጋር የህዳሴውን ግድብ ተከትሎ ካሉ ወሳኝ ጉዳዮች ጋር በስፋት መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።
ሁለቱ አመራሮች በተጨማሪም በሳዑዲ አረቢያ ስለሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ተነጋግረዋል።
ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የተደረጉ ውይይቶችንና የተገኙ ወጤቶችን  በተመለከተም አቶ ገዱ ለአምባሳደሩ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣
አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላሂንም ሳዑዲ አረቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠው፣ ሁለቱ አገሮች ከላቸው የካበተ የዲፕሎማሲ ልምድ አንጻር የአቅም ግንባታ ልውውጥ በማድረግ ላይ አተከረው እንዲሠሩ ሀገራቸው ትኩረት ሰጥታ እንደምትንቀሳቀስ አረጋግጠዋል።
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሦስቱ ሀገራት ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱና የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ወደሚያረጋግጥ መስመር እንዲገቡ ሳዑዲ አረቢያ ድጋፍ እንደምትሰጥ አምባሳደሩ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY