60 ሺኅ አባወራዎችን ለማገዝ የ116 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

60 ሺኅ አባወራዎችን ለማገዝ የ116 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በድህነት ውስጥ የሚገኙ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኑሯቸው ላይ ችግር እንዳይፈጠር ለማገዝ 116 ሚሊየን ብር የእርዳታ ድጋፍ ስምምነት ተደረገ።

የድጋፍ ስምምነቱን የከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ሚኒስቴር እና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዩኒሴፍ ጋር የተፈራረሙት ሲሆን፣ የገንዘብ ድጋፉ የተገኘው ከስዊድን መንግሥት መሆኑ ታውቋል።
በፕሮግራሙ ከ60 ሺኅ በላይ አባዎራዎች እንደሚደረግ እና ለ6 ወራት እንደሚቆይ ተጠቁሟል ቐ። ድጋፉ በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የሚውል ነው ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም ምግብ ድርጅት ለሚያጠቡ እናቶች የሚሆን የ11 ሚሊየን ብር ድጋፍ  ለ6 ተከታታይ ወራት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY