በኢትዮጵያ ዛሬ 245 የኮሮና ተጠቂዎችና የ7 ሰዎች ሞት አስመዘገበች

በኢትዮጵያ ዛሬ 245 የኮሮና ተጠቂዎችና የ7 ሰዎች ሞት አስመዘገበች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገሯ ከገባ በኋላ ከፍተኛ የተባለውን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛውን ቁጥር አስመዘገበች።

ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ5ሺኅ 709 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ፣ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ድምርም 2ሺኅ 915 ደርሷል።
ዛሬ  በምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው 241 ኢትዮጵያዊያንና 4 የውጭ ሀገር ዜጎች እንደሆኑ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ መግለጫ ያሳያል።
በኮቪድ 19 ቫይረስ ከተያዙት ሰዎች መካከል 172 ወንድና 73 ሴት ሲሆኑ፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 85 አመት ነው ያለው መግለጫ፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከልም 190 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 15 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 17 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል እንደሆነም  ያሳያል፡፡
በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በቫይረሱ ምክንያት ተጨማሪ የ7 ኢትዮጵያዊያን ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ 6ቱ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው እና አንዱ ደግሞ በሕክምና ማዕከል ሕክምና ሲከታተሉ እንደነበረም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በመሆኑም አጠቃላይ በአገሪቱ በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 47 መድረሱን ያመላከተው ሚኒስቴሩ፤ በአንጻሩ ትላንትና 17 ሰዎች (16 ከአዲስ አበባና 1 ሰው ከደቡብ ክልል) ከበሽው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 451 እንደ ደረሱም ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY