ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ውስጥ ከለውጥ በፊት በነበሩት ሁለት ዓመታት ክልሎች የተመጣጠነ ውክልና እንዳልነበራቸው አዲስ የተሾሙት የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ገለፁ።
በቅርቡ አፈ ጉባዔ ሆነው የተሾሙት አቶ አዳም ፋራህ ከለውጥ በፊት ክልሎች ሚዛናዊ ውክልና በሀገሪቱ እንዳልነበራቸው ጠቁመው፤ የክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር ሁኔታም መሸራረፍ የሚስተዋልበት እንደነበርና ከሁለት ዓመት ወዲህ ይህ ችግር በሂደት እየተቀረፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ቀደም ሲል ታዳጊ በሚል የሚጠሩ ክልል ተወላጆች በፌዴራል የሥልጣን እርከን ያላቸውን ውክልናን በማጣቀሽነት ያቀረቡት አዲሱ ተሿሚ፤ በቀጣይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሀገራዊ ማንነትንና ብሄራዊ ማንነትን ባጣጣመ መልኩ እንዲሠራ ጥረት እንደሚደረግ፣ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ መስጠትና ራስን በራስ የማስተዳደር ሥርዓት እንዲጎለብት እንደሚደረግም አስረድተዋል።