ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኮሮና ቫይረስ በርካታ ዜጎቻቸውን በሞት በማጣት ክፉኛ የተቀጡት የአውሮፓ ሀገራት የኮሮናን ቫይረስ የሚከላከለው ክትባት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲገኝ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ናቸው ተባለ።
አሁን ላይ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዮት ከሆነ የአዉሮጳ ሀገራት ” አስትራዜኔካ” ከተባለዉ ተቋም ጋር የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት አቅርቦትን በተመለከተ ስምምነት ፈጽመዋል።
የጣልያን የጤና ሚንስቴር እንደ ገለፀው ፈረንሳይ፣ጣሊያን፣ጀርመንና ኔዘርላንድ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድኃኒትን አስትራዜኔካ ከተባለዉ ተቋም ጋር በፈጸሙት ዉል መሰረት ለአዉሮጳ ሀገራት ዜጎች እንደሚያቀርቡ ያስታወቀው የጣልያን የጤና ሚኒስቴር፤ በዉሉ መሰረት ፋብሪካው 400 ሚሊየን ዶዝ የክትባት መድኃኒትን ለሀገራቱ ያስረክባል ብሏል።
በእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በመሠራት ላይ ነው የተባለለትን የክትባት መድኃኒት የመጀመሪያዉ ዙር አቅርቦት የተያዘዉ ዓመት 2020 ሳይጠናቀቅ በሥራ ላይ ይውላል መባሉም ታውቋል።