እስከሁን ለ192,087 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል ዛሬ ተጨማሪ 109 ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል 

እስከሁን ለ192,087 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል ዛሬ ተጨማሪ 109 ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ፤ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

ዛሬ ሟች  ሆና የተመዘገበችው ሰው የአዲስ አበባ  ነዋሪ የሆነች  የ45 ዓመት ሴት ስትሆን ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠው በአስክሬን ምርመራ ነው።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ዉስጥ ለ5 ሺኅ 102 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ፤ 109 ኢትዮጲያዉያንና አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መሀል 60 ወንዶች፣ 49 ደግሞ ሴቶች እንደሆኑና እድሜያቸዉ ከ1 እስከ 78ዓመት እንደሚደርስ የገለፀው የጤና ሚኒስቴር ፤
81 ሰዎች የአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች የኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች የትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች የአፋር ክልል ፣ 4 የሶማሌ፣ 3 ሰዎች የአማራ ክልል እና 2 ሰዎች የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውንም አረጋግጧል።
እስካሁን በኢትዮጵያ ምርመራ የተደረገለቸው ሰዎች ቁጥር
 192,087  መድረሱ ታውቋል።

LEAVE A REPLY