ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በብሮድካስት ባለሥልጣን የቀረበው የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ረቂቅ ላይ ተጨማሪ ውይይት እንዲደረግበት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጠይቀዋል ተባለ።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የመገናኛ ብዙኃን የሚመራበትን ራሱን የቻለ ፖሊሲ እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል፣ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግብዓት እንዲሰጡበት አድርጓል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ አስፈላጊነትን የገለፁ ሲሆን፣ በረቂቅ ሰነዱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ሐሳብ ሰጥተውበታል፡፡
ከመገናኛ ብዙኃን ማስፈፀሚያ ስትራተጂዎች እና ከመገናኛ ብዙኃን ባለቤትነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ፓርቲዎቹ ያነሱ ሲሆን፤ ፓርቲዎቹ የሚዲያ የመገናኛ ብዙኃን ከማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ጋር ያለውን ፋይዳ በመጠቆም ተጨማሪ ውይይቶችና ምክክሮች እንዲካሄዱበትና አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በውይይቱ የብሮድ ካስት ዋና ዳይሬክተር ከሚዲያ ባለቤትነትና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና ምክረ ሐሳቦች ሠፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።