የድንበር ተሻጋሪ አሾከርካሪዎች በኅብረተሰቡ በሚደርስባቸው ተፅዕኖ ጫካ ውስጥ ለማደር ተገደዱ

የድንበር ተሻጋሪ አሾከርካሪዎች በኅብረተሰቡ በሚደርስባቸው ተፅዕኖ ጫካ ውስጥ ለማደር ተገደዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ከኅብረተሰቡ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ።

የድንበር ተሻጋሪ መኪኖች አሽከርካሪዎች በጉዟቸው ወቅት በሚያቋርጧቸው ኢትዮጵያ ከተሞች እና በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ መገለል እየደረሰባቸው በመሆኑ ሥራ ለመልቀቅ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ክብረት አለማየሁ እንደገለጹት ከሆነ፤ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች፣ በጉዟቸው ወቅት ከዚህ ቀደም ተሸከርካሪዎችን በማቆም ዕረፍት ያደርጉባቸው በነበሩ ከተሞች እንዳያርፉ በነዋሪዎች መገለል እንደ ደረሰባቸው ይፋ አድርገዋል።
ይህንን ከኅብረተሰቡ የሚመጣውን ጫና በመፍራት እነዚህ የድንበር አቋራጭ ከባድ መኪና አሾከርካሪዎች፤ በጫካ ውስጥ አቁመው ሰው በሌለባቸው አካባቢዎች ለማረፍና ለማደር  እንደሚገደዱ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY