ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አቶ ኢብራሒም ዑስማን በቅርቡ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው የተሾሙት አቶ አደን ፋራህን በመተካት የሶማሌ ክልል ምክትል ርእስ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።
በቅፅል ስማቸው “ማንዴላ” የሚባሉት አቶ መሎው ኢብራሒም አብዲ ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው መመረጣቸውም ተሰምቷል።
በለውጡ አስቀጣይና የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሐመድ ዑመር የሚመራ የብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ ባካሔደው ሰብሰባ፤ ሠፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ሁለት አዳዲስ ሹመቶችን እንዳፀደቁ ታውቋል።
በስብሰባው በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙትን አቶ አደም ፋራህ ቦታ በመተካት አቶ ኢብራሒም ዑስማን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
በተጨማሪም አቶ መሎው ኢብራሒም አብዲ (ማንዴላ) ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።
ይህም ሹመት በቀጣይ ለሶማሌ ክልል ምክር ቤት እንደሚቀርብ የሶማሌ ክልል ኮሙዮኒኬሽን አብዶ ሂሎው ሐሰን ተናግረዋል።