የደቡብ ክልል ም/ቤት ጉባዔ የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ ወሰነ

የደቡብ ክልል ም/ቤት ጉባዔ የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ጉባዔ የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ የወሰነው የሥልጣን ርክብክብ እንዲደረግ የቀረበለት አጀንዳ ላይ ከተወያየ በኋላ እንደሆነም ተሰምቷል።
ከዚህ በመነሳት ነባሩ የደቡብ ክልል በአዲስ መልክ ለሚዋቀረው ለሲዳማ ዞን የሥልጣን ርክክብ በይፋ እንደሚደረግም በምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ ተነግሯል።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ የተካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ ሲዳማ በሀገሪቱ ዐሥረኛው ክልል  ሆኖ መመዝገቡ  ይታወቃል።
በደቡብ ክልል ሌሎች አካባቢዎችም እየተነሱ ያሉ የመዋቅር ጥያቄዎች በተገቢው መልኩ እንዲታይ መንግሥትና የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ አቅጣጫ እንዳስቀመጠም ለማወቅ ተተችሏል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት ከ2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ ሠፊ ምክክር በማድረግ አፅድቆታል።

LEAVE A REPLY