ዛሬ በተደረገ 399  ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ዛሬ በተደረገ 399  ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገሪቱ ከገባ ከሦስት ወር በኋላ ሪከርድ የሆነውን በቫይረሱ የተያዙ ሰውችን ቁጥር አስመዘገበች።

የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ከሆነ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ለ4 ሺኅ 848 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 22 (8 ከጤና ተቋም እና 14 ከማኅበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን፣ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም ተብሏል።
በተያያዘ መረጃ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሌ ክልል፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1ሺኅ 122 ደርሷል።

LEAVE A REPLY