ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሰላም ሚኒስቴር ለሁሉም ዜጎች የሚሠራ ብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከተባለ የህንድ ተቋም ጋር መፈጸሙን ገለጸ።
የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የሙከራ ትግበራ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።
በስምምነቱ መሠረት ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ዘመናዊ የአሰራር ሲስተም የሚዘረጋ ሲሆን፤ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ለማድረግ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በርካታ ክንውኖች ሲካሄዱ መሰንበታቸውን ወ/ሮ ሞፈሪያት ካሚል አረጋግጠዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ አገልገሎት የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚረዳ፣ ወንጀል ከመከላከልና የፋይናንስ ዘርፉን ከማዘመን አኳያም ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
በሙከራ ትግበራው 30 ሺኅ ዜጎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ የሙከራ ትግበራው ከስምንት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።