ዛሬ 63 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ፣ ሦስት ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል

ዛሬ 63 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ፣ ሦስት ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ4 ሺኅ 457 የላብራቶሪ ምርመራ ሥድሣ  ሦስት (63) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

በዚህ መሠረት በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4 ሺኅ 532 ደርሷል።
ከተደረገው ጠቅላላ የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ፤ 18 (5 ከጤና ተቋም እና 13 ከማኅበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን፤ ከአንድ የ75 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የጤና ሚኒስትር አስታውቋል።
በሌላ በኩል በለይቶ በሕክምና ማዕከል ውስጥ ክትትል ላይ የነበረች የ34 ዓመት ሴት፤ የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕይወቷ ያለፈ ሲሆን፤ በጠቅላላ ሁለት ሰዎች በ24 ሰዐት ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።
እስካሁን  በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሠባ አራት (74) መድረሱን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል።
በተያያዘ ዜና ትናንት ዘጠና አንድ (91) ሰዎች (67 ከአዲስ አበባ፣ 16 ከሶማሊ ክልል፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1ሺኅ 213 ደርሷል።

LEAVE A REPLY