በአ/አ እየተሠሩ ስላሉ ፕሮጀክቶች መረጃ ለማግኘት የሚያስችል ማዕከል ተከፈተ

በአ/አ እየተሠሩ ስላሉ ፕሮጀክቶች መረጃ ለማግኘት የሚያስችል ማዕከል ተከፈተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሐሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማዕከል መከፈቱን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ገለፀ።

አዲሱ ማዕከል መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የካፌና ዋይፋይ የተዘጋጀለት መሆኑም ተሰምቷል።
በማዕከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከት፣ የራሱን ሐሳብ በጽሑፍና በድምፅ መስጠት የሚችል ሲሆን፤ የተሰጡትንም አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው እንደሚያቀርቡ ተነግሯል።
የማዕከሉ መቋቋም የከተማዋ ነዋሪ በከተማዋ ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲጨምርና ስለ ከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠር፤ ብሎም ግልፅነት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።
.

LEAVE A REPLY