ፓርላማው ነገ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ስለመስጠት የወጣውን ህግ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል

ፓርላማው ነገ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ስለመስጠት የወጣውን ህግ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል

PM Netanyahu addressing the Ethiopian parliament

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛው መደበኛ ስብሰባ ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ  የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመት መርምሮ ማጽደቅ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለመመደብ የቀረበ የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ማፅደቅ ተቀዳሚ አጀንዳዎቹ እንደሆኑ ታውቋል።
 የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን፣ ማጽደቅ፣ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅም ተሰምቷል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በኳታር መንግሥት የማዕድን ሥራዎች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅንም የነገው የምክር ቤት አባላቱ ውሎ ይገመግመዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንዲያግዝ ለሁለተኛው የኢትዮጵያ የዕድገትና ተወዳዳሪነት የልማት ፖሊሲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማፅደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ከመመርመር ባሻገር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ስለመስጠት የወጣው ሕግ በሥራ ላይ እንዲውል ሊያፀድቀው እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።

LEAVE A REPLY