ምርጫ ቦርድ በህወሓት በኩል የቀረበውን የምርጫ ላካሂድ ጥያቄ እንደማይቀበል አረጋገጠ

ምርጫ ቦርድ በህወሓት በኩል የቀረበውን የምርጫ ላካሂድ ጥያቄ እንደማይቀበል አረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅለትም ሆነ ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበለው መሆኑን ፣ የተጠየቀውን የሰው ኃይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የህግ አግባብም እንደሌለ ይፋ አደረገ።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ኮቪድ 19ኝን እየተከላከለ 6ኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የወሰነ በመሆኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ምርጫውን  እንዲያስፈፅም፣ ምርጫውን ለማካሄድ  የሚያስፈልግ የሰው ኃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ መጠየቁን ያስታወሰው ምርጫ ቦርድ፤ ጥያቄውን እንዳልተቀበለው ገልጿል።
“ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ እያለ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባገራችንም በመከሰቱ ምርጫውን ለማስፈፀም ሲያካሂዳቸው የነበሩት ሥራዎች እንደተስተጓጎሉ ይታወቃል፡፡ ወረርሽኙ በኢትዮጵያ መከሰቱ እንደተረጋገጠ ሁናቴውን መገምገም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቦርዱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ 6ኛውን አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ  ቀደም ሲል ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ ማካሄድ እንደማይችል አስታውቋል” ያለው በብርቱካን ሚዴቅሳ የሚመራው ምርጫ ቦርድ፤ በትግራይ ክልል የቀረበውም ጥያቄ ከዚህ አሳማኝ ምክንያትና ከሕግ አግባብ ውጪ እንደማይታይ ባወጣው መግለጫ ላይ አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY