በቀን ሁለት ሚሊየን ዳቦ ያመርታል የተባለው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ዛሬ በይፋ ተመረቀ

በቀን ሁለት ሚሊየን ዳቦ ያመርታል የተባለው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ዛሬ በይፋ ተመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሰዐት ሰማኒያ ሺኅ፣ በቀን ሁለት ሚሊየን ዳቦ እንደሚያመርት የተገነረለት ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ መጠናቀቅ ዳቦ ከማምረት ባሻገር የብልጽግና ጉዞ መጀመሩን የሚያመላክት ነው ያሉት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ፤ የፕሮጀክቱ ምረቃ በምግብ ራስን በመቻል፣ ከድሕነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት የሚያጎላና እየተሠሩ ባሉ ሥራዎች ጥያቄ ለሚያነሱ አካላት ምላሽ የሚሰጥ ነው ብለዋል።
‘በኢትዮጵያ ፋብሪካ ጀምሮ መጨረስ የተለመደ እንዳልነበር የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ዳቦ ፋብሪካን ሚድሮክ ኩባንያ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቁ አድናቆታቸውን ከመስጠት ባሻገር ምስጋናም አቅርበዋል።
በፋብሪካው የምረቃ ሥነ ሥርዐት ላይ ከም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ጋር ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ በማንኛውም ዘርፍ ትኩረት መስጠት በአጭር ጊዜ ውጤታማ እንደሚያደርግና  ይህም ለሌሎች ተግባራት አርአያ መሆኑን ምስክርነት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ለምግብነት የሚውሉ በርካታ ፍጆታዎችን አገሪቱ በውጭ ምንዛሪ እያስገባች በመሆኑ፤ እንዲህ ዓይነት ፋብሪካዎች መቋቋማቸው ፋይዳቸው የጎላ ነው እንደሆነ ተነግሮለታል።
ስንዴን በአገር ውስጥ ምርት ብቻ ለመሸፈን እንዲቻል በአፋር በአዋሽ ተፋሰስ፣ በኦሞ ተፋሰስ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኦሞና በሱማሌ ክልል ሰፋፊ የስንዴ እርሻዎች በዚህ ዓመት መጀመራቸውን የተናገሩት ዐቢይ አሕመድ፤ በተጨማሪም 20 ሺኅ ሄክታር ማልማትና ከእያንዳንዱ ሄክታር የተሻለ ምርት መሰብሰብ የሚያስችል ልምድ የተወሰደ በመሆኑ፣ በቀጣይ ዓመትም ከ100 ሺኀ ሄክታር በላይ የማምረት እቅድ መያዙን አብራርተዋል።
ሀገሪቱ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታትም ስንዴን ከውጭ ማስመጣትን ለማቆም ፍላጎት እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት ለሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ያቀረበው ዘመናዊ የዳቦ ማሽን አቅርቦትም ተቀባይነት ማግኘቱን እና በዚህም በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች መሰል የዳቦ መጋገሪያ ማሽን በድጋፍ ለማበርከት ቃል መገባቱን አስታውቀዋል።
ዛሬ የተመረቀው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን ዳቦዎች ለኅብረተሰቡ የሚያከፋፍሉ የተደራጁ ወጣቶችና ለመሸጫነት የሚያገለግሉ ሥራ ያቆሙ 400 አንበሳ አውቶቢሶች መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

LEAVE A REPLY