በኢትዮጵያ 250 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፣ የሁለት ሰው ሞተዋል 

በኢትዮጵያ 250 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፣ የሁለት ሰው ሞተዋል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ5ሺኅ 514 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 250 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5ሺኅ 425 ደርሷል።

ዛሬ ከተደረገው ጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 32 (11 ከጤና ተቋም እና 21 ከማኅበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን፤ 6 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ዕለታዊ ሪፖርቱ ያሳያል።
በሌላ መልኩ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት ማለፉም ተነግሯል።
በተያያዘ ዜና ትናንት 144 ሰዎች (123 ከአዲስ አበባ፣ 7 ከአማራ ክልል፣ 7 ከትግራይ ክልል፣ 5 ከሶማሊ ክልል፣ እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1ሺኅ 688 መድረሱ ታውቋል።

LEAVE A REPLY