የጠ/ሚ/ር ዐቢይ መንግሥት ኢትዮ ቴሌኮምን መሸጡን እንዲያቆም ኢዜማ አሳሰበ

የጠ/ሚ/ር ዐቢይ መንግሥት ኢትዮ ቴሌኮምን መሸጡን እንዲያቆም ኢዜማ አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ገዥዉ ፓርቲ (ብልፅግና) የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለውን ጥድፊያ በአስቸኳይ እንዲያቆም ኢዜማ አስጠነቀቀ።

በርካታ ኢትዮጵያውያን በሰከነና በሳል በሆነ የፖለቲካ አካሄድ እየተጓዘ ነው የሚባልለት ኢዜማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ግዙፍ የልማት ድርጅቶችን ለመሸጥ የሚያደርገውን ሩጫ በፍጥነት ሊያቆም ይገባዋል ሲልም መክሯል።
  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ ገዥዉ ፓርቲ (ብልፅግና) በተለይም የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመሸጥ እያደረገዉ ያለዉ ሂደት ግልጸኝነት የጎደለዉና ጥድፊያ የተሞላበት ነዉ ብሏል፡፡
“የኢኮኖሚ ዘርፎች ተወዳዳሪነት ዋነኛ ሞተር የሆነን የቴሌኮም ኢንደስትሪ እንደ ተራ መረጃ ማስተላለፍያ ብቻ በማየት፤ ለውጪ ድርጅት ለመሸጥ የጀመረው መንገድ ፍፁም አደገኛ እና የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል” ሲል ጉዳዮን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠየቀ ተመልክናል፡፡

LEAVE A REPLY