ከአዲስ አበባ ናቸው የተባሉ ወጣቶች እንቦጭን ለመታደግ ወደ ጣና ጉዞ ጀመሩ 

ከአዲስ አበባ ናቸው የተባሉ ወጣቶች እንቦጭን ለመታደግ ወደ ጣና ጉዞ ጀመሩ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በጎ ፍቃደኛ የሆኑና የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው የተባሉ ወጣቶች እንቦጭ አረምን ለማስወገድ ወደጣና ሀይቅ ሊሄዱ ነው ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሓላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንደገለጹት፤ በድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት “ጣናን እንታደግ” በሚል መርህ ጣና ሀይቅን የወረረውን የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ወደ ባህርዳር ከተማ እንደሚጓዙ አረጋግጧል።
የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በጠቅላለው 100 በላይ ልዑካን በድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ እንደሚሆኑ የገለጹት ሓላፊው፤ በጎ ፍቃደኞቹ በቆይታቸው የእንቦጭ አረምን ከማስወገድ በተጨማሪ በባህርዳር ከተማ የጽዳት እና የትራፊክ አገልግሎት እንደሚያከናውኑም አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አዘጋጅነት፣ በድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከዚህ ቀደም ሲል በአዳማ ፣በደብረ ብረሃን እና በአምቦ ከተሞች የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰጠ መሆኑን ሰምተናል።
ቀደም ባሉት ዓመታት “አምላኪ መለስ” ነው በሚባለው ታጠቅ ካሳ ይመራ የነበረውና የኢሕአዴግ ሰላማዊ ሰልፎችና ስብሰባዎች አድማቂ የነበረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር፤ ከለውጡ ማግሥት አንስቶ በአደረጃጀት ቅርፁን ለውጦ ከተለያዮ የኦሮሚያ ከተሞች በመጡ ወጣቶች እንዲሞላ መደረጉን የጠቆሙ ታማኝ የዜና ምንጮቻችን ይህ ስብስብ አሁን ላይ በከተማዋ ስም የሚደረጉ የወጣቶች ተሳትፎዎችን በብቃት እንዲወጣ ከታከለ ኡማ አስተዳደር ቀጥተኛ ድጋፍና ፖለቲካዊ እገዛ እየተደረገለት እንደሚገኝ ነግረውናል።

LEAVE A REPLY