ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፋት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ 5 ሺኅ 552 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታወቀ።
ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺኅ 570 ደርሷል።
በአንጻሩ ባለፋት 24 ሰዐታት 5 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ መሆኑን ተከትሎ በሀገራችን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰውች ቁጥር 90 ደርሷል።
በተያያዘ ዜና በትናንትናው ዕለት 327 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ብዛት 2015 አድርሶታል፡፡