ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፋት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ3 ሺኅ 895 የላብራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር አስታወቀ።
ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺኅ 689 መድረሱ ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል በሀገሪቱ ባለፋት 24 ሰዐታት ውስጥጨ4 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ፤ ይህን ተከትሎ በሀገራችን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርን 98 ደርሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትናው ዕለት 117 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ብዛት 2 ሺኅ 132 እንዳደረሰው ለማወቅ ተችሏል።