ኦቢኤን ሁለተኛ ቻናልና የተለያዮ የኦሮሚያ ከተሞች የሚደመጡ ኤፍ ኤም ራዲዮችን አስመረቀ

ኦቢኤን ሁለተኛ ቻናልና የተለያዮ የኦሮሚያ ከተሞች የሚደመጡ ኤፍ ኤም ራዲዮችን አስመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኦሮሚያ ብሮድ ካስት ኔትዎርክ (ኦቢኤን ) ሁለተኛ ቻናል የሆነውን ሆርን ኦፍ አፍሪካ እና ኦቢቫን ቴክኖሎጂውን፣ ኤፍ ኤም ራዲዮችን አስመረቀ።

ድርጅቱ  ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያዎችን ያስመረቀው በወሊሶ፣ አምቦ እና  ባሌ ሮቤ ከተሞች  መሆኑም ታውቋል።
በምረቃ ስነ – ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የተለያዩ ክልሎች  ፕሬዝዳንቶች፣ የፌደራል ከፍተኛ አመራር፣ እንዲሁም የኦቢኤን መስራች እና  የቀድሞው  የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አባዱላ ገመዳ ተገኝተዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናቡ አስራት፤ ኦቢኤን ዛሬ ከደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ  የራሳቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ  አቶ አባ ዱላ ገመዳ እና ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
 ድርጅቱ ከያዘው ራዕይ አንፃር በአሁኑ ሰዐት እያሰራጨ  ካለው በስምንት የተለያዩ ቋንቋዎች ከሚቀርብ ፕሮግራም በተጨማሪ  በሀገር ውስጥ የሚነገሩ ሌሎች ቋንቋዎችን በቅርቡ ለማሰራጨት ማቀዱ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY