ከኮሮና በኋላ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን “ሸን ገን” ቪዛ...

ከኮሮና በኋላ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን “ሸን ገን” ቪዛ አገኘች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን  የሸንገን ቪዛ ፍቃድ ካገኙ 11 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ተነገረ።

እንደ አረቢያን ገልፍ ዘገባ ከሆነ በህብረቱ ሸንገን ቪዛ ፍቃድ ከተሰጣቸው 54 የዓለም ሀገራት መካከል ከአፍሪካ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ግብፅ፣ ሞሪሺያስ፣ ሞሮኮ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያና ዛምቢያ ይገኙበታል ።
በኮሮና ምክንያት ድንበሮቻቸውን ዘግተው የቆዩት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት እ.ኤ.አ ከሀምሌ 1፣ 2020 ጀምሮ ድንበሮቻቸውን ሲከፍቱ ኢንዲገቡ ፍቃድ ከተሰጣቸው ሀገራት መካከል እንደ አሜሪካ እና ብራዚል ያሉ ወረርሽኙ ያገረሸባቸው ሀገራት እንዳልተካተቱም መረጃው ያሳያል።
አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ጀማይካ እና ኩባ ወደ አውሮፓ ኢንዲገቡ ፍቃድ ካገኙ 54 አገራት መካከል ይገኛሉ ያለው ዘገባ፤
ሸንገን ቪዛ አብዛኛውን የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ውስጥ ተጓዦች ያለገደብ አንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የቪዛ ዓይነት እንደሆነም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY