የአ/አ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ከተማዋን ሊጠቀልሏት በሚቋምጡ ኃይሎች ዙሪያ በዝግ እየተገማገሙ ነው

የአ/አ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ከተማዋን ሊጠቀልሏት በሚቋምጡ ኃይሎች ዙሪያ በዝግ እየተገማገሙ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢሕአዴግ ከስሞ የተመሰረተው  የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የ2012 ዓ.ም አፈፃፀምን በአዳማ እየገመገሙ መሆናቸው ተሰማ።

በመድረኩ ከለውጥ በኋላ የብልጽግና ጉዞ ጅማሮ እንዴት እየሄደ ነው? የሚል እና ያገጠሙ ችግሮች ለምን እንደተፈጠሩ፣ እንዴትስ ተፈቱ? የሚሉ ጉዳዮችም ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል የሚሉ መረጃዎችን የተለያዮ የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ወቅታዊው የመዲናዋ የጸጥታ፣ የፖለቲካ ሁኔታ፣ የኮሮና ወረርሽኝና የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያም በጥልቀት ውይይት እንደሚደረግ የተገለጸ ቢሆንም የጉባዔው ተሳታፊ የሆኑና ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው ልጆች ከዚህ በዘለለ አመራር አባላቱን እያወዛገበ ያለ ወሳኝ ነጥቦች መኖራቸውን ይናገራሉ።
በለውጡ ማግስት ህወሓትን ገፍተው ከመንበረ ሥልጣኑ ያባረሩት ኦዴፓ እና አዴፓ (ኦህዴድና ብአዴን) ዋና መዲናዋ አዲስ አበባን ለማስተዳደር ከስምምነት ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጊዜያዊ የከተማዋ  ከንቲባ አድርገው ከሾሟቸው በኋላ ወሳኝ ቦታዎች በኦዴፓ አባላት መያዛቸው በሁለቱ ፓርቲዎች መከፋፈልን ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ በዐሥሩ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ሠባቱ ክፍለ ከተሞች ከላይ እስከ ታች አመራር በኦዴፓ አባላትና በኦሮሞ ተወላጆች መጥለቅለቁ በቀድሞው የብአዴን አመራር አባላት ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ እንደነበር የገለጹት ታማኝ ምንጮቻችን፤ ይህ ውዝግብ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶቹ ፈራርሰው በአንድ ወጥ ፓርቲነት ወደ ብልፅግና ከመጡ በኋላ ነገሩ የተዳፈነ መስሎ መቆየቱን አስታውቀዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ (በተለይም ባለፉት አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ) ከተለያዮ የኦሮሚያ ከተሞች የሚመጡ ወጣቶች በወረዳና ክፍለ ከተሞች ውስጥ ሆን ተብሎ በስፋት እንዲመደቡ መደረጉ፣ በከተማዋ ያሉ ክፍት ቤቶችም ለኦሮሚያ ተወላጆች በወረራ መልክ እንዲያዝ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር መደረጉ የአማራ ተወላጆች በየሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና አመራሮች እስካሁን ድረስ  ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲያሰሙ አድርጓል።
በአሁኑ ሰዐት ግልፅ የሆነ የተረኝነት ፖለቲካ በከተማዋ እየተራመደ መሆኑን ያመኑ የብልፅግና አመራሮች በዛሬው ግምገማ ላይ አንድ ብሔር ተኮር የሆነ የሠራተኛ ቅጥር እና የሰፈራ ሁኔታ ስለተከናወነበት ምክንያት  በቂ ማብራሪያ እንዲቀርብና በቀጣይም ይህ ዓይነቱ አሠራር እንዲቀር መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ነገ ታማኝ ምንጮች  ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY