የደምቢዶሎ ዮንቨርስቲ ሴት ተማሪዎችን ለኦነግ ሸኔ አሳልፈው የሰጡ 17 ሰዎች ላይ ክስ...

የደምቢዶሎ ዮንቨርስቲ ሴት ተማሪዎችን ለኦነግ ሸኔ አሳልፈው የሰጡ 17 ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ከታገቱ ከስምንት ወራት በላይ ጊዜን ያስቆጠሩት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እገታ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ።

ትናንት ሐምሌ 10/2012 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ” ሦስት የሽብርተኝነት”  ክስ የተመሰረተባቸው ሰዎች 17 ሲሆኑ፤ የክስ መዝገቡም እነከሊፋ አብዱራህማን በሚል እንደተመዘገበ ተገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው የደንቢ ዶሎ ተማሪዎችን አግተዋል በሚል ዐቃቤ የእገታና የጠለፋ ሽብር ወንጀልን ጠቅሶ ነው ክስ መስርቶባቸዋል።
በተጨማሪም በተጠርጣሪዎቹ ላይ  ከተከሳሾቹ መሀል አንዱ ተማሪዎቹ በጫካ ውስጥ እየተጓዙ ስለመሸባቸው፣ ታጋቾች መሆናቸውን እያወቀ ቤቱ በማሳደሩና ሁኔታውን ለየትኛውም የመንግሥት አካል ባለማሳወቁ፤ የሽብር ወንጀልን ባለማሳወቅ ክስ የሚል ክስ ተመስርቶበታል።
ለፍርድ ቤቱ በቀረበው ክስ ላይ ተማሪዎቹ ወደ አማራ ክልል በአንድ መኪና በመጓዝ ላይ ሳሉ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ ሰዬ እና አንሰሎ ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ከመኪናው በማስወረድ እየደበደቡ ጫካ ውስጥ ለሚገኙ የኦነግ ሸኔ አመራሮች አሳልፈው መስጠታቸው ተገልጿል።
ትናንት በዋለው ችሎት ሠባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ሲገለጽ፣ ሁለቱ በኮሮና ቫይረስ በመጠርጠራቸው ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ተከትሎ የቀሩት ተከሳሾች በፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ችሎቱ አዝዟል።
 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በችሎቱ የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ከጠበቃቸው ጋር ተመካክረው እንዲቀርቡና ክሳቸው እንዲሰማ ለሐምሌ 30/20 12 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ ተበትኗል።

LEAVE A REPLY