በአማራና ኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የሰብኣዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ...

በአማራና ኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የሰብኣዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አመነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አምነስቲ ኢንተርናሽናል  በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አሉ ሲል ከሳምንታት በፊት ያወጣው መግለጫን አስመልክቶ ምላሽ የሰጠው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መግለጫው በከፊል ትክክል ነው ሲል አመነ።

ሪፖርቱ ከመውጣቱ በፊት መንግሥት ለማረጋገጥ ምርመራ ሲከናወንባቸው የነበሩ ጉዳዮች ናቸው በአምንስቲ የተገለጹት ያለው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፤ የጸጥታ ኃይሎች በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ያደረሱትን ጥፋት አስመልክቶ ዓለም ዐቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በግንቦት ወር ያወጣው ሪፖርት ከፊል እውነታን ያዘለ መሆኑን ባደረግሁት ማጣራት አረጋግጫለሁ ብሏል።
በወቅቱ አምንስቲ ያወጣውን  መግለጫና የድርጅቱን ሪፖርት ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ያላደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በዚህም መሰረት በዘገባው ውስጥ ከተካተቱት የመብት ጥሰት ወቀሳዎች የተወሰኑት በከፊልም ቢሆን ተዓማኒነት ያላቸው ሆነው መገኘታቸውን መስክሯል።
 “ከእነዚህ በከፊል ተዐማኒነት ካላቸው ጉዳዮች መካከል በርካቶቹ በመንግሥት ታውቀው ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የምርመራ ሥራ ሲከናወንባቸው የነበሩ ናቸው” የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምላሽ፤ በተጨማሪም ሪፖርቱ ገለልተኛነት የጎደለው፣ ተዓማኒነት የጎደላቸው የሆኑ ምስክርነቶችን በመያዝ እጅግ ውስብስብ በሆኑ ግጭቶችና የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ላይ በመድረስ፣ በሕግ ማስከበር ሂደት በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎችን የመብት ጥሰት አድርጎ አቅርቦ ነበር ሲልም አምንስቲን በተወሰነ ደረጃ ተችቷል።

LEAVE A REPLY