በአሁኑ ሰዓት የኦሮሞ ህዝብ ነፃ አወጣሃለሁ በሚለው ቄሮ በተባለ ከድንጋይ እስከእጅ ቦንብ በታጠቀ ቡድንና ኦነግ ሸኔ በተባለ ነፍጥ የታጠቀ ቡድን የታገተና የመናገር የመምረጥ አስተያየት የመስጠትም ሆነ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተከባብሮና ተፋቅሮ የመኖር መብቱን፣ የመማርና ልጆቹን በሰላም የማሳደግ ነፃነቱን፣ ሰርቶ የመለወጥና ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብቱን የተነጠቀ ህዝብ ሁኗል፡፡ እንደሰሜን ኮሪያው አምባገነን መሪ ዱላ በተሸከመ የመንደር ጎረምሳ ህዝቡ የት ላይ ማጨብጨብና የት ላይ ማልቀስ እንዳለበት እየተነገረው የሚኖር ሚስኪን ህዝብ ሁኗል!
ለምሳሌ አንድ ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖር ኦሮሞ ‹‹ቄሮ የሚያደርገው ነገር ልክ አይደለም ›› ብሎ ቢናገር ምን ይጠብቀዋል?…ያው ገጀራ ነው! አንድም ኦሮሞ (የመንግስት ሰው ካልሆነ በስተቀር ) በራሱ ምድር ላይ ቀና ብሎ ያመነበትን የመነጋር ነጻነት የለውም፤ ያለው አማራጭ መንግስትን መስደብ መዝለፍና ቄሮ የሚባል መንጋ የሚነዱት ሰዎች የጠሉትን መጥላት የወደዱትን መውደድ ነው፡፡ ብዙሃኑ ኦሮሞ ኦሮሚያ ወደየት እየሄደች እንደሆነ ሆዱ ያውቃል… ቢችል ወደመሃል አገር አልያም ወደውጭ ቢሰደድ ምርጫው ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን የቆሸሸ ነብሰ ገዳይነትና አጥፊነት ፈፅሞ የማይቀበል እንደውም የሚፀየፈው ቁጥር የትየለሌ ነው ግን… ታግቷል አንገቱ ላይ ገጀራ ተደቅኖበታል …ውጭ አገር እንኳን ቢኖር እዛ አገር ቤት ለቤተሰቡ ደህንነት ይፈራል!
በድንጋይና በገጀራ የተጨፈጨፈ ሬሳ በየመንገዱ የሚወድቅበት ክልል ላይ ማን ልጆቹን ማሳደግ ይፈልጋል ?… በየቀኑ የሰው ንብረት ውድመትና ዘረፋ በጠራራ ፀሓይ የሚታይበት ሲኦል ውስጥ ማን መኖር ይፈልጋል?…. አስተምሬ ዶክተር ኢንጅነር ይሆንልኛል ያለው ልጁ ድንጋይና ዱላ ተሸክሞ በየመንገዱ ሆ ሲል ማየት የሚፈልግ ወላጅ ማነው? …ይችን ቢተነፍሳት ግን የሚከተለውን ስለሚያውቅ ያለው አማራጭ አብሮ መንግስትን ሲረግምና ሲሰድብ መዋል ነው …መንግስት እንደቄሮ ጨፍጭፎ አይገድለውማ ! ብዙሃኑ የቄሮ እስረኛ መንግስትን ሲሳደብና ሲዘልፍ የሚውለው ጀግና ስለሆነ አይደለም …ቄሮን ለመናገር ስለሚፈራ እንጅ!
ዛሬ ቀላል የማይባሉ የኦሮሞ ወጣቶች ከመማርና ሰርተው ሕይወታቸውን ከመለወጥ ይልቅ በየመንገዱ ዱላ ተሸክመው ሲጃጃሉና እድሜ ልካቸውን የሚያቅበዘብዛቸውን የሰው ደም ሲያፈሱ፣ ንብረት ሲያወድሙ ይውላሉ! ማንም ወላጅ ልጁ ነብሰ ገዳይ እና ዘራፊ እንዲሆን አይፈልግም …ግን ደግሞ በራሱም ልጅ ማዘዝ አይችልም ፡፡ ዛሬ ኦሮሚያ ላይ እንኳን መጥፎ ድርጊትን ማውገዝ ዝም ማለትም መሃል ሰፋሪ የሚያስብል ጉዳይ ሁኗል …ለዛም ነው የሀይማኖት አባቶች አባ ገዳዎች ሳይቀሩ መንጋውን ‹‹ተው›› ማለት የፈሩት! የኦሮሞ አባ ገዳዎችም ሆኑ የሃይማኖት አባቶች ተሰሚነታቸውም ሆነ አቅማቸው በቄሮ ተነጥቆ ስማቸው ብቻ ነው የቆመው ! ተው ቢሉ መንጋው ፊቱን ወደነሱ ማዞሩ አይቀሬ ነው ፡፡
ቄሮ አመጠዋለሁ የሚለውን ነፃነት አመጣሁ ቢል እንኳን በሀይል ሁሉን ነገር ማግኘት የለመደ ሜንታሊቲ በመነጋገር በመግባባት እና በችሎታ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ ነገ ይሄ መንጋ በራሱ ስንፍና ከአስሩ ሶስት ቢያመጣ የአስተማሪውን አንገት በገጀራ ለመቅላት አይመለስም …ነገ ይሄ መንጋ አንዲት ሴት ለፍቅር ጠይቆ እምቢ ብትለው አልያም ለጋብቻ ሽማግሌ ልኮ ወላጆቿ ባይስማሙ እሷን በድንጋይ ካለወገርኩ ቤቷን ከነቤተሰቧ ካላቃጠልኩ ማለቱ አይቀሬ ነው ….ነገ ይሄ መንጋ ስራ ተወዳድሮ ቢወድቅ የቀጣሪውን ድርጅት ካላወደምኩ ብሎ ጋዝና ክብሪት ይዞ መሄዱ ያማይቀር ነው!
ሐይል የሁሉምነገር መፍትሄ፣ የጀግንነት መገለጫ እንዲሁም ሕይዎትን የመቀየሪያ አቋራጭ መንገድ እንደሆነ እየተሰበከ አድጓላ! ተው አታጥፋ የሚለው ሁሉ ጠላቱ ነው …ነፃነቱን የሚጋፋ ነው ፡፡ እውነትን የመቀበል አቅሙ ተሰልቧል፣ እውነት ማለት በነፃነት ትግል ስም በባርነት አንቀው የሚመሩት አጥፊዎች የሚነግሩት በልኩ የተሰፋለት ተረት ብቻ ነው ፡፡ ለምን አይልም ፣ እንዴት አይልም ካለም የመንጋ ወገራ ይጠብቀዋል፡፡
ዛሬ ላይ ኦሮሞ የራሱን ልጆች በመፍራት በአደገኛ ባርነት ውስጥ ነው፡፡ ያለው አማራጭ ሌላኛውን ልጁን ሲሰድብና ሲረግም መዋል ብቻ ነው ! አንድ ቀን ግን ሞትን የማይፈሩ ጀግና ኦሮሞዎች ይነሳሉ … ምድራቸው ላይ የሚፈነቸውን ነብሰ ገዳይ መንጋ እንደዝንብ በማስተዋልና በዕውቀት ጭራ በትነው ….ተወዳዳሪ ሃሳብ ብቻ ይዘው ብቅ የሚሉ፣ በራሳቸውም ልጆች ይሁን በሌሎች ጫና ስር ሁነው ግራ የገባው ጥፋት ከመደገፍ ወጥተው እውነትን ብቻ የሚመለከቱ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ክብር ያላቸው፣ እልቂትና ግፍ ምንም እንደማይፈይድ የሚረዱ ኦሮሞዎች ይነሳሉ …
ያኔ ኦሮሞ በነፃነት ትግል ስም ለባርነት በሚያጩት ገዳዮችና ጨፍጫፊዎች ሳይሆን በተፈጥሮ ሰብዓዊነቱና የነፃነት ፍላጎቱ የሰው ልጅ ሁሉ ዙሮ ሊያያት እንኳን የምታሳቅቅ የጥፋት ክልል ሳይሆን ሊያዩዋት የሚናፍቋት ከወንድምና እህቶቹ ጋር በፍቅር የሚኖር ህዝብ ምድር ያደርጓታል ፡፡ ዛሬ ላይ ምንም ብትሉ እንረዳችኋለን በቄሮ ባርነት ስር ናችሁና !