የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት በ11 ወር 37 ማሊዮን ዶላር አግኝቻለሁ አለ

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት በ11 ወር 37 ማሊዮን ዶላር አግኝቻለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ  (ባለፉት 11 ወራት) 37 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ።

የውጭ ምንዛሬው የተገኘው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ (ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ) ምርቶችን ወደ ሠላሣ ሀገራት በመላኩ እንደሆነም ተነግሯል።
የኢንስቲትዩት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ እንዳስታወቁት፤ የምርቶቹ የገበያ መዳረሻ ከጎረቤት አገራት ጀምሮ እስከ አውሮፓና አሜሪካ በመዝለቅ በዕቅድ ዘመኑ 30 አገሮች የሀገራችንን ምርቶች ተቀባይ ለማድረግ መቻሉን የኢንስቲትዮቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ ገልጸዋል።
የ2012 በጀት ዓመት የዐሥራ አንድ ወራት ዕቅድ 55 ሚሊዮን 748 ሺኅ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ እንደ መኪና፣ ሞባይል፣ አልሙኒየም፣ ቆርቆሮ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ወደ ተለያዩ አገሮች ለመላክ ግብ በማስቀመጥ ወደ እንቅስቃሴ መገባቱን ተከትሎ፤ ከተላከው ምርት የተገለጸው ከ37 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገባትጨተችሏል።
በመሠረታዊ ብረታ ብረት በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብት 14 ሚሊዮን 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለመላክ ታቅዶ 3 ሚሊዮን 409 ሺህ ዶላር እንደተገኘ ያመላከተው የሓላፊው መግለጫ፤ በኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ 41 ሚሊዮን 247 ሺኅ ዶላር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም  33 ሚሊዮን 593 ሺህ በላይ መላኩን አረጋግጧል።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የኤክስፖርት ምርቱ የቀነሰ ሲሆን፤ ቀደም ሲል የምንዛሬ እጥረት በመኖሩ ምክንያት ኢንዱስትሪዎቹ የአቅማቸውን ያህል አምርተው ለገበያ እያቀረቡ እንዳልነበረ አስታውሰው፤ የኩባንያዎቹ ግብዓት ከውጭ የሚመጣ በመሆኑና በተለያየ ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ምርት ማምረት አለመቻሉም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY