በኢትዮጵያ በግለሰብ የተሠሩ ሁለት ድሮኖች መጀመሪያ ጊዜ ህጋዊ ፍቃደኛ ከመንግሥት አገኙ

በኢትዮጵያ በግለሰብ የተሠሩ ሁለት ድሮኖች መጀመሪያ ጊዜ ህጋዊ ፍቃደኛ ከመንግሥት አገኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያዊው ወጣት ናኦል ዳባ የተሠሩ ሁለት  ድሮን (ፀረ-አረም መድኃኒት መርጫና ከርቀት ሆኖ ለማኅበረሰቡ መልክዕት ማድረስ የሚያስችሉ)፣ አንድ የኮሮና ቫይረስ ሙቀት መለኪያ የፈጠራ ውጤቶች ይፋ ሆኑ።

በወጣቱ የተሠራውና ለጸረ-አረም መርጫ የሚያገለግለው ድሮን 10 ሊትር የመያዝ አቅም ያለው ከመሆኑ ባሻገር፣ በአንድ ጊዜ 65 ሄክታር መሬት መርጨት ያስችላል፡፡ በቀጣይም በሞዴሉ እስከ 500 ሊትር የመያዝ አቅም የሚኖረው እንደሆነም ከወዲሁ ተነግሮለታል።
የፈጠራ ሥራውን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ፤ ሁነኛው እስካሁን በድሮውን ዘርፍ ፈቃድ የሚሰጥበት አሠራር እንዳልነበረ  ጠቁመው፤ አሁን አሠራሩን የሚፈቅድ ህግ መርቀቁን ተከትሎ የፈጠራ ባለቤቱ ወጣት ናኦልና ሌሎች መስፈርቱን አሟልተው ሲገኙ ፈቃድ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY