ራይድ እና ፈረስ የተሰኙት ሁለት የትራንስፖርት ኩባንያዎች በኢንተርኔት መቋረጥ 400 ሚሊዮን ብር...

ራይድ እና ፈረስ የተሰኙት ሁለት የትራንስፖርት ኩባንያዎች በኢንተርኔት መቋረጥ 400 ሚሊዮን ብር አጥተናል አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ጋር ተያይዞ በተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት የተለያዮ ታላላቅ የንግድ ተቋማት ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረጉ መሆናቸውን ገለጹ።

በዚህ መንገድ ላልተገባ ኪሳራ ተዳርገናል ካሉት የግል የንግድ ተቋማት መሀል በታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩት ድርጅቶች ቀዳሚ ሆነዋል። በአዲስ አበባ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖት አገልግሎት ከሚሰጡት ዘመነኛ ኩባንያዎች መሀል  ራይድ እና ፈረስ የተሰኙት የትራንስፖርት ተቋማት በሁለት ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ ኪሳራ ገጥሞናል ብለዋል።
ሁለቱ ተቋማት እንደ ገለጹት ከሆነ የኢንተርኔት መቋረጡን ተከትሎ  በ15 ቀናት ብቻ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አጥተዋል።
አሁን ላይ የዋይፋይ አገልግሎት መጀመሩን ተከትሎ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሥራ እንቅስቃሴ መኖሩን ቢገልጹም የኢንተርኔት አገልግሎቱ በተቋረጠበት ወቅት ግን  በሥራቸው የሚተዳደሩ በብዙ ሺኅ የሚቆጠሩ አሽከርካሪዎች ሥራ ለመፍታት እንደተዳረጉ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY