የአፍሪካ ሕብረት አባላት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቪዲዮ ኮንፍረስ ዛሬ ተወያዮ

የአፍሪካ ሕብረት አባላት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቪዲዮ ኮንፍረስ ዛሬ ተወያዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአፍሪካ ሕብረት አባላት ቢሮ መሪዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ መምከራቸው ተሰማ።

የአፍሪካ ሕብረት አባላት ቢሮ መሪዎች ባሳለፍነው ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትኄን ማበጀት ዙሪያ ውይይት እንዳደረጉ ይታወሳል።
የዛሬው ውይይት ባሳለፍነው ሰኔ 19 የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የተካሄደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚካሄደውን ስብሰባ እንደመሩት ታውቋል።
በስብሰባው የቢሮው አባላት የሆኑት የኬንያ፣ የዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የማሊ መሪዎች እና ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸው ተሰምቷል።
የአፍሪካ ሕብረት አባላት ቢሮ በዛሬው ስብሰባው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያደርጉት በነበሩት የሦስትዮሽ ድርድር የደረሱበትን ደረጃ የሚመለከት መሆኑ ታውቋል።

LEAVE A REPLY