ሕዝብን የሚያጋጩ፣ የሃይማኖት ጥቃት በሚፈጽሙ ላይ ሠራዊቱ እርምጃ እንደሚወስድ ኢታማዦር ሹሙ አስታወቁ

ሕዝብን የሚያጋጩ፣ የሃይማኖት ጥቃት በሚፈጽሙ ላይ ሠራዊቱ እርምጃ እንደሚወስድ ኢታማዦር ሹሙ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም ሲሉ  የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሐመድ ገለጹ።

የሠራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም ኢታማዦር ሹሙ ተናግረዋል።
“ከህግ ውጪ ሆኖ፤ በተለይም በሕዝቦች መካከል ቁርሾና ግጭት በመፍጠርጨሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ሥራዎችን ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት፣ ወደ እልቂት ያመራሉና መንግሥት እርምጃ ይወስዳል” ያሉት ጀነራል አደም መሐመድ፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ መንግሥት እርምጃ መውሰድ ካልቻለ የመንግሥትነት ተልዕኮው ምን ሊሆን ይችላል?  ሲሉም ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል።
“ግልጽ መሆን ያለበት መንግሥትና የመከላከያ ሠራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያየ ዝም አይልም ፡፡ ይህን ማስቆም በህገ መንግሥቱ የተሰጠው ሓላፊነት ነው ። የሠራዊቱም ተልዕኮ ይሄ ነው፡፡ መንግስትም ቢሆን የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሓላፊነት ፤ ግዴታም አለበት” በማለት ሥርዓቱ ሕግን ለማስከበር ያለውን ቁርጠኝነት ይፋ አድርገዋል።
 የሠራዊቱ ተልእኮ የሚመነጨው ከሕገ መንግሥቱ በመሆኑም ተልእኮውን ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ጋር አይይዞ ማየት ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፤ ሕዝቡም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰቦችን ሊታገል እንደሚገባም ገልጸዋል።
“የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያውያንን እኩል ሊያገለግል የሚችል ተቋም ሆኖ እየተገነባ ነው። የጸጥታ ተቋማት የማንም ፓርቲ እሴት ወይም ሀብት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ሀብት ናቸው ” በማለት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ላይ የገለጹት ጀነራል አደም መሐመድ፤ በሠራዊቱ ውስጥ ለነበሩ በርካታ የሠራዊት የግንባታ ጥያቄዎች ብዙ ኪሳራዎች ነበሩም ብለዋል።

LEAVE A REPLY