የሠባት ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር ጀምረዋል ተባለ

የሠባት ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር ጀምረዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና በሽታ ከተከሰተ በኋላ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት ማሳየቱን ተከትሎ ሠባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር  ጀመሩ።

ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ክብረአብ በአሁኑ ወቅት በአየር ትራንስፖርት የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ቁጥር በአሁኑ ሰዐት ሠባት መድረሱን አረጋግጠዋል።
በአማካይ በቀን ሠባት የውጭ ሀገራት አየር መንገድ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ እንደሆኑ የጠቆሙት ሓላፊው፤ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ በዓለም ላይ ከተስፋፋ በኋላ የበርካታ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን በረራ ለማቆም መገደዳቸው ይታወሳል።
አሁን ላይ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መብረር ከጀመሩ አየር መንገዶች መካከል የዱባይ ፣ የቱርክ፣ የኳታር፣ የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኬንያ እና የጅቡቲ አየር መንገዶች ቀዳሚዎቹ መሆኑ ነው የተነገረው።
በዚህ መሠረት በአማካይ ሁለት መደበኛ በረራ እና አምስት መደበኛ ያልሆኑ የመንገደኛ አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እየበረሩ እንደሆነ ታውቋል።

LEAVE A REPLY